ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

Debre Metemaqe Saint Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

ማስታወቂያ/Announcement

የ2024 የጥምቀት በዓል አከባበር ታቦት በ5:00pm ከቤተክርስቲያናችን መንቀሳቀስ ስለሚጀምር ቀድመን ተገኝተን በማጀብ ወደ ባሀረ ጥምቅቱ

Read More »

የጥበቃና ደጀሰላም ተረኞች

የአራት ሳምንት የጥበቃ ተረኖች፡ August 6th Girma Liyew August 13thSolomon Desu August 20thMerid Tadesse August

Read More »

Gospel in English

Please use the Facebook link below to watch the weekly gospel in English which was

Read More »

About Us

በአሪዞና ፊኒክስ እና አካባቢዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን መኖር ከጀመሩ ከአራት አስርት አመታት በላይ ይሆናል። ማንም ክርስቲያን አካባቢውን ሲቀይር ቤተክርስቲያን ይኖር ይሆን ብሎ መጠየቁ የተለመደ ነው። ሆኖም በወቅቱ የኢትዮጵያውያን ቁጥር ጥቂት በመሆኑና የመገናኘት እድልም ስላልነበረ ሁሉም በየቤቱ ከመጸለይ በላይ ምንም ማድረግ አልቻሉም ነበር። ቤት ከመቀመጥ ደግሞ ቋንቋው ባይገባቸውም ከምንም ይሻላል በሚል ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም እየሄዱ ይገለገሉ ነበር። በዓይን ከመተያየት አልፎ ሰላምታ መለዋወጥ ብሎም ወደ መመካከር የዘለለው የኢትዮጵያውያኑ ግንኙነት በቋንቋቸው ወደመገልገል ተሸጋግረዋል።  Read More …

የደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በፊኒክስ አሪዞና የ20 ዓመታት ጉዞ

ጊዜው የአሪዞና ዓየር ወደ ነበልባልነት የሚቀየርበት፣ ከሚከንፍ መኪና በቀር እግረኛ ለዓይን የማይታይበት፣ ዓየሯ ምግብ ከሆነባት እናት ኢትዮጵያ ለመጣ ደግሞ ሃገሩን ከገሃነመ እሳት የሚቆጥሩበት ሞቃት ግዜ ነበር::

ቅዳሴ፣ የቤተ ክርስቲያን እጣን ጭስና ዝማሬ የናፈቀው የሃገሬ ህዝበ ክርስቲያን መድረሻ አጥቷል:: ሐበሻ እዚህ ቦታ አለ ᎐᎐᎐ አዲስ ሰው መጣ ᎐᎐᎐ ሲባል የሚሮጥበት ᎐᎐᎐ ዘመድ ወገን፣ የሃገር የወንዝ ልጅ የሚናፈቅበት ዘመን ነበር::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ባልና ሚስት፣ ጓደኛ ውይይታቸው ሁሉ ቤተ እግዚያብሄርን ስለ ማግኘት ነበር:: እርስ በእርስ የሚተዋወቅ ᎐᎐᎐ጓደኛ ከዘመድ ተቆጣጥረው ተጠራርተዋል:: ቁጥራቸው ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው::

ያ ዘመን ሁለት ሆነው በካሴት ቅዳሴ ሥርዓት የተከወነበት፤ ከተከራዩበት አዳራሽ በ ”ሰዓት አልፏል” የሚባረሩበት፣ ገንዘብ ለመሰብሰብ በረዶና አይስ ክሪም ለመሸጥ ሲንከራተቱ ለገበያ ሳይበቃ በአሪዞና ቃጠሎ በረዶው ቀልጦ እናቶችን ለኪሳራ ያበቃበት ዘመን ነው::  Read More …

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

በመልአከ ገነት መምህር ሰሎሞን ዓለሙ

መግቢያ

ጥናት (አጠናን) ሲባል በቃል መያዝን ብቻ ሣይሆን በተግባር ማሣየትንም ያካትታል።

የኮርሱ ዓላማ

ዘለዓለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል በጥሩ አነሳስ ወይም አጀማመር የሰው ልጅ በቃልና በኑሮው እንዲሁም በተግባር እያጠናው እንዲጠቀምበትና እንዲጠቅምበት የአጠናኑን መክፈቻ ቁልፍ መስጠት ወይም በሩን ማሣየት ነው።
ኢያ 1፥8፣ ዘዳ 6፥6፣ ኤፌ 6፥7፣ ሮሜ 15፥4፣ ጢሞ 3፥16-17. Read More …

5452 S 17th Dr.
Phoenix, AZ 85041

Phone: (602) 580-8719
Email: admin@ethiomariam.org